Editor-in-Chief @AmjamboAfrica, Founder @MeseretMedia and @EthiopiaCheck, Former @AP reporter in Ethiopia

United States
My colleagues and I had the privilege of meeting with the Maine Secretary of State in Augusta today. What a truly humbling experience!
3
2,017
ከሰሞኑ መንግስት ብስለቱን ያሳየባቸው እና አሁንም የሚዳክርባቸው ጉዳዮች! በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በድጋሜ የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ መንግስት በአንድ በኩል ብስለቱን በግልፅ አስመስክሯል። እሱም የዛሬ ስድስት አመት እንደነበረው ህዝብን ከታጣቂ ባለየ መልኩ 'ቁረጠው፣ ማጎርያ ካምፕ አስገባው፣ በልተኸው ተቀደስ፣ ጭራቅ ናቸው' ወዘተ ከሚል ህዝብን ቂም ውስጥ ከቶ ከመንግስት ከሚያራርቅ ንግግር እና ፕሮፖጋንዳ ራሱን አርቋል። ይህ አካሄድ በዛሬው የጠ/ሚሩ ንግግር ላይ ተንፀባርቋል፣ የህዝብን ድጋፍ የሚያስገኝ አካሄድ መሆኑ ግልፅ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ሚድያዎች ስራቸውን በነፃነት እንዳይሰሩ የሚደረገው አፈና ልክ እንደዛሬ ስድስት አመቱ ተባብሶ ቀጥሏል። የሚድያ ባለስልጣናት ጋዜጠኞችን እየሰበሰቡ 'ይህን እንዳትፅፉ፣ ያንን እንዳታናግሩ' የሚል ግብስብስ ነገር ውስጥ ገብተዋል፣ ከዛም አልፈው ባለፉት ጥቂት ቀናት ጋዜጠኞችን አስረዋል። ጥፋት ካለ በሚድያ ህጉ መዳኘት እያለ ዘሎ ጋዜጠኞችን ማነቅ ምን የሚሉት አባዜ እንደሆነ የሚያውቁት ራሳቸው ናቸው። ለማንኛውም ሰላም ለመላው ህዝባችን።
16
4
83
13,561
#FactCheck በነገራችን ላይ ፕሬዝደንት ታዬ አፅቀስላሴ ከሰሞኑ በተመድ ስብሰባ ላይ መሳተፋቸውን ተከትሎ "በአለም አቀፍ መድረክ ተዋረዱ" እና ሌሎች በርካታ መልዕክቶችን አንዳንድ አለም አቀፍ 'ተንታኞች' እና አክቲቪስቶች አንድ ቪድዮን በማቅረብ እያሰራጩ ይገኛሉ። ቪድዮው ግን የአሁን ሳይሆን የዛሬ አራት አመት የእርስ በርስ ጦርነት በተካሄደበት ወቅት የተቀረፀ ነበር። እውነት ነው ሁኔታው በወቅቱ የሚያሳፍር ነበር... በወቅቱ የተመድ ዋና ፀሐፊ እንዲህ አይነት ንግግር ለአንድ የመንግስት ተወካይ ተናግረው አያውቁም ተብሎ ነበር። ከሰሞኑ የምናየው ጦርነት ከቀጠለ ሊደገም ይችላል፣ እውነታው ግን ቪድዮው የአሁን አለመሆኑ ነው። የቆየውን ቪድዮ በዚህ ሊንክ ማየት ይቻላል: facebook.com/share/v/1WZUN4G…
14
10
58
16,784
Hello Chicago! "Kaleidoscope Live! 2026: Policy x Power x Pathways" conference happening tomorrow and Tuesday. Representing our LM-Network (Amjambo Africa).
1
7
3,925
meseretmedia.org/p/mma እነዚህን ስፖርተኞች እንደ ምሳሌ (role models) አድርገው ለሚመለከቱ ህፃናት እና ወጣቶች የምናስተላልፈው መልዕክት ምንድነው?
26
1
28
11,763
የዛሬ 5 ወር ገደማ ለስራ ወደተዛወርኩበት ሜይን ግዛት በገባሁ በነጋታው ለቡና ቁጭ ባልኩበት ካፌ ሮቤልን ተዋወቅኩት፣ መልካም ሰው መሆኑን ለመረዳት ግዜ አልፈጀብኝም፣ በዛኑ ጠዋት ተወውቀን ለምሳ ቤቱ ይዞኝ ሄደ። በዚህ ወቅት ነበር የካንሰር ተጠቂ መሆኑን እንባ ባዘሉ አይኖቹ ያጫወተኝ። ከዛ ወዲህ በብዛት እንደዋወል ነበር። የዛሬ አንድ ወር ገደማ ግን "ዶክተሮች አንድ ወር ግዜ ብቻ ነው ያሉህ አለኝ" በማለት ነገረኝ፣ ወዲያው ቤቱ ሄጄም አገኘሁት። ኢትዮጵያ ሄዶ የህይወቱን መጨረሻ ቀናት ማሳለፍ እንደሚፈልግ ነግሮኝ ተሰነባበትን። ከዛ ወዲህ ስልኩ አይሰራም፣ ተጠፋፋን። ከኢትዮጵያ ተመልሶ እንደነበር እና እዚሁ ማረፉ ትናንት ተነገረኝ። ዛሬ ቀብሩ ፖርትላንድ ከተማ ውስጥ ተፈፀመ። ሮቤል በ19 አመቱ የዛሬ 20 አመት ገደማ ነበር ወደ አሜሪካ የመጣው፣ የሁለት ሴት ልጆች አባትም ነበር። ነብስህ በሰላም ትረፍ ወንድሜ!
14
2
156
11,955
Me: “Just one lamb for Enkutatash.” Farmer: “Say no more.” Brings the excavator. ገመድ ፍለጋ የለ፣ እግር ያዝልኝ የለ 😊
5
2
111
7,694
ፖርትላንድ፣ ሜይን ውስጥ ከኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ወዳጆች ጋር የአዲስ ዓመት ዋዜማን አሳለፍን። እንኳን አደረሳችሁ! መልካም አዲስ ዓመት! Happy Ethiopian New Year!
4
2
81
8,876
ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ retweeted
On Friday, the United Nations General Assembly adopted an African proposal for a new world map, which shows countries’ true size relative to one another. In favor: 164 Against: 1 Abstentions: 6
712
3,162
14,315
3,118,002
ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ retweeted
ሰላም።
126
49
435
81,836
ሜርላንድ ግዛት እያለሁ በሐዋርድ ካውንቲ ውስጥ ባለ የጥቁሮች ታሪክ ዙርያ ለ 'Beacon' ሚድያ የፃፍኩት ትንታኔ ሽልማት አስገኝቷል፣ ሽልማቱ በቴነሲ ግዛት በቅርቡ። That was a surprise! Thank you 🙏🏽 ፅሁፉን ለማንበብ: thebeaconnewspapers.com/unea…
24
9
198
15,185
አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ያሳያል የተባለ አንድ ቪድዮ ሲዘዋወር ተመለከትኩ፣ ቪድዮውን የለጠፉት ሰዎች ደግሞ 'የቀድሞው የክልል ፕሬዝደንት አሁን ላይ ይህን ስራ አሜሪካ እየሰሩ ነው' በሚል ለማሸማቀቅ ያሰቡ ይመስላል። ቪድዮው የእውነት ከሆነ ትክክለኛ መልዕክቱ ግለሰቡ እንደ ሌላው ሳይዘርፉ፣ በውጭ ሀብት ሳያካብቱ እንዲሁም በዱባይ፣ በናይሮቢ፣ በአውሮፓ እና በአሜሪካ የህዝብ ሀብት ይዘው እንዳልሸሹ፣ አሁን ላይ ደግሞ በነፃ ህሊና ስራ ሰርተው እየኖሩ እንደሆኑ የሚያሳይ ነው። ይህን መልዕክት የለቀቁ ሰዎች ስራ ሰርቶ ከሚኖር አንድ ባለስልጣን ከነበረ ግለሰብ ይልቅ የህዝብን ሀብት ዘርፎ ዱባይ ላይ ቪላ በመግዛት የሚንደላቀቅ ባለስልጣንን አክብረው እና አድንቀው የሚኖሩ ለመሆናቸው ምስክር አይሻም።
65
118
768
51,509
ፎቷቸውን ትኩር ብዬ ተመለከትኩት፣ ህይወታቸው ገና ከፊታቸው የሚጠብቃቸው ወጣቶች እንደሆኑ ያስታውቃሉ። መሀል ላይ ያለው ወጣት ድንጋጤው ይጋባል፣ ሰው ባላጠፋው ጥፋት ሲከሰስ የሚሰማው ስሜት። ሁሉም 'ፋኖ ናችሁ' ተብለው ተረሸኑ፣ አስከሬናቸው እንኳን እንዳይነሳ ለቀናት ተከለከለ። ተመስገን ጌታቸው፣ ይታገሱ አሰግደው፣ ግዛው ግርማዬ! ነፍስ ይማር!
#ዜናመሠረት በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ሶስት ወጣቶች 'ፋኖ ናችሁ' ተብለው ከመኪና እንዲወርዱ ከተደረጉ በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ መረሸናቸው ታወቀ ተመስገን ጌታቸው፣ ይታገሱ አሰግደው እና ግዛው ግርማዬ የተባሉ ሶስት የአማራ ክልል ተወላጆች ከተሳፈሩበት የሕዝብ ማጓጓዣ መኪና ላይ “ፋኖ ናችሁ” በሚል ውንጀላ ተገደው እንዲወርዱ ከተደረጉ በኋላ በግፍ መገደላቸውን የአካባቢው ምንጮች ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል ተጨማሪ ያንብቡ: meseretmedia.org/p/346
32
73
188
18,184
መንግስትን መቃወም እና የህዝብ ተቋማትን ማጥቃት ሙሉ በሙሉ የተለያዩ ነገሮች ናቸው! እንደ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ንግድ ባንክ ያሉ የህዝብ ሀብቶች ላይ ያተኮሩ ጥቃቶች ድንቁርና ካልሆኑ ምን ሊባሉ ይችላሉ? መንግስታት ይመጣሉ፣ ይሄዳሉ: ተቋማቱ ግን የህዝብ ሆነው ይኖራሉ። የሀገራችንን ሰንደቅ አላማ ይዞ አለምን የሚዞርን ታላቅ አየር መንገድ አርማ መሬት ላይ ጥሎ መርገጥ ከቀውስነት የዘለለ ትርጉም ያለው አይመስለኝም።
33
13
140
29,317
ከአሜሪካዋ Maine ግዛት ዋና ገዢ (Governor) ጃኔት ሚልስ ጋር ትናንት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ቃለ-መጠይቅ አርጌ ነበር፣ ዝርዝሩን ከታች ይገኛል ⤵️ amjamboafrica.com/amjambo-ex…
7
7
28
8,464
የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ፣ አሁን ላይ ደግሞ በአሜሪካ የግዙፉ Delta Air Lines ስትራቴጂክ አማካሪ የሆኑት አቶ ተወልደ ገብረማርያም ከአየር መንገዳችን ከለቀቁ ወዲህ የመጀመርያውን ሰፊ ቃለ መጠይቅ ከ LTM- Network/Amjambo Africa ሚድያችን ጋር ቆይታ አድርገዋል። ሙሉው ቃለ መጠይቅ ከቀናት በኋላ በድረ-ገፃችን እና ሶሻል ሚድያ ገፆቻችን ላይ ይለቀቃል፣ ይጠብቁን amjamboafrica.com ፌስቡክ: facebook.com/share/1JeWXnEfk… ኤክስ: x.com/AmjamboAfrica ዋትሳፕ: Follow the Amjambo Africa channel on WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VbC… ኢንስታግራም: instagram.com/amjamboafrica?…
#AmjamboHighlight | From transforming Ethiopian Airlines into an unprecedented global powerhouse to shaping international strategy at Delta Air Lines, Tewolde Gebremariam’s journey is a masterclass in the "can-do" (Yichalal) spirit. In the upcoming August edition of Amjambo Africa, we sat down with the visionary architect of African aviation to discuss shattering corporate myths, successfully navigating historic industry crises, and his powerful advice for diaspora professionals competing on the world stage. Keep an eye out for the full exclusive interview hitting stands and our website in just a few days! Photo: The Reporter Newspaper #AmjamboAfrica #AfricanAviation #EthiopianAirlines #DeltaAirLines
14
16
117
89,398
'ሀገር እየመከረ ነው' በሚባልበት ወቅት ንፁሀን ዜጎች ላይ እንዲህ አይነት የጭካኔ ተግባር በድሮን መፈፀም መልዕክቱ ምንድን ነው?
#ዜናመሠረት በአባይ ግዮን ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም ላይ ዛሬ ጠዋት የድሮን ጥቃት ተፈፅሞ ምግብ ሲያዘጋጁ የነበሩ እናቶች መገደላቸው ተሰማ የአይን እማኞች ለሚድያችን ዛሬ ምሽት በስልክ እንደገለፁት ጠዋት 4:30 ላይ የተፈፀመው ጥቃት ያነጣጠረው በገዳሙ ውስጥ "ቤተ-እግዚአብሔር" በመባል በሚጠራው እና እናቶች ለምዕመናን ምግብ ለማብሰል በሚጠቀሙበት ክፍል ላይ ነበር። በዚህም ምክንያት የሰው ህይወት አልፏል፣ በርካቶች ቆስለዋል፣ እንዲሁም ህንፃው ሙሉ በሙሉ ፈርሷል ተብሏል ዝርዝሩን ያንብቡ: meseretmedia.org/p/66b
5
3
22
11,295
#የግልምልከታ "ጽምዶ" የተባለው ስብስብ በጋራ ጥቅምና በሰላም ላይ የተመሰረተ ሳይሆን የውስጥ ችግሮችን በኃይል ለመፍታት ከውጭ ኃይል ጋር መጣመርን የመረጠ ሀይል መሆኑን እያሳየ ነው፣ ይህ አካሄድ ደግሞ ታሪካዊ ስህተት እና የሕዝብ እልቂት ምንጭ መሆኑ የማይቀር ነው። የውስጥ የፖለቲካ ልዩነቶችንና ቅራኔዎችን በውይይት፣ በዕርቅና በሰላማዊ መንገድ በሀገር ውስጥ ከመፍታት ይልቅ የውጭ ኃይላትን ጦርና ጋሻ ጋብዞ የገዛ ወገንን ለማስጨፍለቅ ማሰብ እኩይ ተባር ነው። ቀደም ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ከኤርትራ ጋር በመጣመር በራሳችን ሕዝብ ላይ ያደረሰውን ሰብአዊ ቀውስና ስቃይ ስንተች የነበረውም ለዚሁ ነው ምክንያቱም እንዲህ ያሉ አሰላለፎች የሕዝብን ሕልውና የሚያጠፉ፣ ሀገርን ለባዕድ ጣልቃ ገብነት አሳልፈው የሚሰጡና ጠባሳቸው ለትውልድ የማይሻር በመሆኑ ነው። በመሆኑም አሁንም ሆነ ወደፊት ማንኛውም አካል በየትኛውም ስም “ጽምዶ” የሚል ስብስብ ፈጥሮ የሕዝብን ስቃይና መከራ የሚያበዛ ከሆነ በምንም ዓይነት መመዘኛ ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም። የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲባል የሰላማዊ ሰዎችን ሕይወት መገበሪያ ማድረግና ሀገርን ማፈራረስ የታሪክ ተጠያቂነትን ያስከትላል። እውነተኛ መፍትሔ ሊመጣ የሚችለው ከውጭ ኃይላት በሚገኝ የጦር ድጋፍ ሳይሆን በሀገር ውስጥ ኃይሎች መካከል በሚደረግ እውነተኛና ሁሉን አቀፍ ውይይት ብቻ እንደሆነ በጽኑ አምናለሁ፣ ሰላም የሚገነባው በጠመንጃ አፈሙዝ ሳይሆን በሰላማዊ ድርድር ነው።
74
12
103
29,740
ካለፉት ሶስት ወራት ወዲህ በ Editor-in-Chief (ዋና አርታዒ) የስራ መደብ የሙሉ ግዜ ስራ የጀመርኩበት LTM-Network የአሜሪካዋ ሜይን ግዛት ውስጥ በሰባት ቋንቋዎች መረጃ የሚያቀርብ ብቸኛው እና በአይነቱ ትልቁ ጋዜጣ የሆነው የ Amjambo Africa አሳታሚ ነው። አሁን የተቋሙ ዋና ትኩረት የዲጂታል አቅሙን ማስፋት እንዲሆን አቅጣጫ አስቀምጠን እየሰራን ነው፣ አንዱ ደግሞ በወር ሁለት ግዜ *በነፃ* በቀጥታ ወደ አንባቢዎች ኢሜይል የምንልካቸው እና እኔ የማዘጋጃቸው Newsletter ናቸው። ዛሬውኑ ተመዝግበው መረጃዎቻችንን በነፃ ያንብቡ: ሊንክ ⤵️ amjamboafrica.com/newsletter…
Want to stay connected with news that matters? Join the Amjambo Africa community! We're looking to welcome 1,000 new readers to our newsletter family. Get trusted stories, critical updates, and cultural highlights delivered straight to your inbox for FREE! Click the link to sign up today: Https://www.amjamboafrica.co…
17
5
48
36,118